‘ዘርህን ለዘላለም እተክላለሁ፤ ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’ ” ሴላ
በፊትህ ለዘላለም ጸንቶ እንዲኖር፣ አሁንም የባሪያህን ቤት እባክህ ባርክ። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን አንተው ራስህ ተናግረሃል፤ በበረከትህም የባሪያህ ቤት ለዘላለም ይባረካል።”
ለአባትህ ለዳዊት፣ ‘በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከዘርህ አታጣም’ በማለት በሰጠሁት ተስፋ መሠረት ዙፋንህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።
ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ እርሱ ነው። እርሱ ልጅ ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ። ዙፋኑንም በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’
“ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ለዘላለም እንድነግሥ ከቤተ ሰቤ ሁሉ እኔን መረጠ፤ መሪ እንዲሆንም ይሁዳን መረጠ፤ ከይሁዳም ቤት የእኔን ቤተ ሰብ መረጠ፤ ከአባቴ ልጆች መካከል ደግሞ በመላው እስራኤል ላይ እንድነግሥ ፈቃዱ ሆነ።
እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ፤ በማይታጠፍም ቃሉ እንዲህ አለ፤ “ከሆድህ ፍሬዎች አንዱን፣ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።
ወንዶች ልጆችህ ኪዳኔን፣ የማስተምራቸውንም ምስክርነቴን ቢጠብቁ፣ ልጆቻቸው በዙፋንህ ላይ፣ ለዘላለም ይቀመጣሉ።”
ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ ዝናው ፀሓይ የምትኖረውን ዘመን ያህል ይዝለቅ። ሕዝቦች ሁሉ በርሱ ይባረኩ፤ ሕዝቡ ሁሉ ቡሩክ ነህ ይበለው።
ስለ እግዚአብሔር ምሕረት ለዘላለም እዘምራለሁ፤ በአፌም ታማኝነትህን ከትውልድ እስከ ትውልድ እገልጻለሁ።
የዘር ሐረጉን ለዘላለም፣ ዙፋኑንም በሰማያት ዕድሜ ልክ አጸናለሁ።
የዘር ሐረጉ ለዘላለም፣ ዙፋኑም በፊቴ እንደ ፀሓይ ጸንቶ ይኖራል፤
ጌታ ሆይ፤ ባሪያህ እንዴት እንደ ተፌዘበት፣ የብዙ ሰዎችንም ነቀፋ እንደ ታቀፍሁ ዐስብ።
“እነሆ፤ ደግፌ የያዝሁት፣ በርሱም ደስ የሚለኝ የመረጥሁት አገልጋዬ፤ መንፈሴን በርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ለአሕዛብም ፍትሕን ያመጣል።
ከመካከላቸው እጅግ ደካማ የሆነው እንደ ዳዊት፣ የዳዊት ቤትም ፊት ፊታቸው እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር መልአክ፣ እንደ አምላክ ይሆንላቸው ዘንድ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እግዚአብሔር ይከልላቸዋል።
ኢሳይያስም እንዲሁ፣ “በሕዝቦች ሁሉ ላይ የሚነግሠው፣ የእሴይ ሥር ይመጣል፤ በርሱም ሕዝቦች ተስፋ ያደርጋሉ” ይላል።
“እኔ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች እንዲመሰክር መልአኬን ለአብያተ ክርስቲያናት ልኬአለሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፣ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”