ወገን የሌለውንና ድኻውን ታደጉ፤ ከግፈኛውም እጅ አስጥሏቸው።
ለርዳታ የሚጮኸውን ችግረኛ፣ ድኻ አደጉንም ታድጌአለሁና።
እግዚአብሔር ለድኻ ፍትሕን እንደሚያስከብር፣ ለችግረኛውም ትክክለኛ ፍርድን እንደሚሰጥ ዐውቃለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ከጨቋኙ እጅ አድኑት፤ መጻተኛውን፣ ወላጅ የሌለውንና መበለቲቱን አትበድሉ፤ አትግፏቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።