ዝማሬውን ጀምሩ፤ ከበሮውን ምቱ፤ በበገናና በመሰንቆ ጥዑም ዜማ አሰሙ።
መለከት ነፊዎችና ዘማሪዎችም በአንድነት አንድ ድምፅ ሆነው ለእግዚአብሔር ውዳሴና ምስጋና አቀረቡ፤ በመለከት፣ በጸናጽልና በሌሎች መሣሪያዎች ታጅበውም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እግዚአብሔርን እያወደሱ፣ “እርሱ ቸር ነው፣ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” እያሉ ዘመሩ። ከዚያም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በደመና ተሞላ።
መዕሤያ፣ ሸማያ፣ አልዓዛር፣ ኦዚ፣ ዮሐናን፣ መልክያ፣ ኤላምና ኤጽር ቦታቸውን ያዙ፤ መዘምራኑ በይዝረሕያ መሪነት ዘመሩ።
ብርታቴ ሆይ፤ ውዳሴ አቀርብልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ፣ የምትወድደኝም አምላኬ ነህና።
ዐሥር አውታር ባለው በገና፣ በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ ጥሩ ነው።
ከዚያም የአሮን እኅት ነቢዪቱ ማርያም ከበሮዋን አንሥታ ያዘች፤ የቀሩትም ሴቶች ሁሉ ከበሮ ይዘው እያሸበሸቡ ተከተሏት።
ከዚህ በኋላ መዝሙር ዘምረው ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡ።
በመዝሙርና በውዳሴ፣ በመንፈሳዊም ዝማሬ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ በልባችሁ ለጌታ ተቀኙ፤ አዚሙም።
የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ በጥበብ ሁሉ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በማሕሌት፣ በመንፈሳዊም ቅኔ በማመስገን በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።
ከእናንተ መካከል በመከራ ውስጥ ያለ አለ? እርሱ ይጸልይ፤ የተደሰተ አለ? የምስጋና መዝሙር ይዘምር።