ካህናታቸው በሰይፍ ተገደሉ፤ መበለቶቻቸውም ማልቀስ ተሳናቸው።
የተረፉለትም በመቅሠፍት ዐልቀው ይቀበራሉ፤ መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።
ጥምጥማችሁን ከራሳችሁ አታወርዱም፤ ጫማችሁንም አታወልቁም። በኀጢአታችሁ ትመነምናላችሁ፤ እርስ በርስ ታቃስታላችሁ እንጂ ሐዘን አትቀመጡም፤ አታለቅሱምም።
የእግዚአብሔር ታቦት ተማረከ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ተገደሉ።
ወሬውን ያመጣውም ሰው፣ “እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ሰራዊቱም ከፍተኛ ዕልቂት ደርሶበታል፤ እንዲሁም ሁለቱ ልጆችህ አፍኒንና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት ተማርኳል” ብሎ መለሰለት።
የእግዚአብሔር ታቦት ስለ ተማረከ፣ ዐማቷና ባሏም ስለ ሞቱ፣ “ክብር ከእስራኤል ተለይቷል” ስትል የሕፃኑን ስም ኢካቦድ አለችው።
ከዚያም፣ “የእግዚአብሔር ታቦት ተማርኳልና ክብር ከእስራኤል ተለይቷል” አለች።