አንተ ብርሃን ተላብሰህ ደምቀሃል፤ ግርማዊነትህም ከዘላለም ተራሮች ይልቃል።
ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤ ቀስታቸውም ይሰበራል።
አንበሳ ከደኑ ወጥቷል፤ ሕዝብንም የሚያጠፋ ተሰማርቷል፤ ምድርሽን ባዶ ሊያደርግ፣ ከስፍራው ወጥቷል። ከተሞችሽ ፈራርሰው ይወድቃሉ፤ ያለ ነዋሪም ይቀራሉ።
እርሱም በአንበሶች መካከል ተጐማለለ፤ እየበረታም ሄደ፤ ግዳይ መንጠቅን ተማረ፤ ሰዎችንም በላ።
በግራ እጅህ ያለውን ቀስትህን እመታለሁ፤ በቀኝ እጅህ የያዝሃቸውንም ፍላጾች አስረግፍሃለሁ።