Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



መዝሙር 75:9

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔ ግን ይህን ለዘላለም ዐውጃለሁ፤ ለያዕቆብም አምላክ ዝማሬ አቀርባለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዐይኖቹ የራሱን ውድቀት ይዩ፤ ከሁሉን ቻይ አምላክ ቍጣ ይጠጣ።

በሕይወት ሳለሁ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ቆሜ እስከ ሄድሁ ድረስም አምላኬን እወድሳለሁ።

ጽድቅህን በልቤ አልሸሸግሁም፤ ታማኝነትህንና ማዳንህን እናገራለሁ፤ ምሕረትህንና እውነትህን፣ ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም።

ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣ በቀኝ እጅህ ርዳን፤ መልስልንም።

ይህን ስታደርግልኝ፣ በጽዮን ሴት ልጅ ደጅ፣ ምስጋናህን ዐውጃለሁ፤ በማዳንህም ሐሤት አደርጋለሁ።

የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “በቍጣዬ የወይን ጠጅ የተሞላውን ይህን ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ እኔ ወደምልክህም ሕዝቦች ሁሉ ሄደህ አጠጣቸው።

ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽም፤ ከዚያም ጽዋውን ትሰባብሪዋለሽ፤ ጡትሽንም ትቈራርጪአለሽ፤ እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች