ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፣ ወይም ከምድረ በዳ አይመጣምና፤
ወፍራምና ጠንካራ ጋሻ አንግቦ፣ ሊቋቋመው ወጥቷል።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን የምትከልል ጋሻ ነህ፤ ክብሬንና ራሴንም ቀና ቀና የምታደርግ አንተ ነህ።
በኀይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፤ እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ። ሴላ
መዳፉን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ከንቱ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር። “ጕራውም ፋይዳ አይኖረውም።