አምላክ ሆይ፤ ጠላት የሚያሾፈው እስከ መቼ ነው? ባላንጣስ ለዘላለም በስምህ ያላግጣልን?
ይህም ከሚዘልፍና ከሚያላግጥ ሰው ድምፅ የተነሣ፣ ከጠላትና ከተበቃይ ሁኔታ የተነሣ ነው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤
ጌታ ሆይ፤ ጎረቤቶቻችን በአንተ ላይ የተዘባበቱትን መዘባበት፣ ሰባት ዕጥፍ አድርገህ አስታቅፋቸው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን? ቍጣህስ እንደ እሳት የሚነድደው እስከ መቼ ነው?
የሰደብኸውና ያቃለልኸው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ከፍ ያደረግኸው፣ ዐይንህን በትዕቢት ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው እኮ!
ከእነርሱም አንዱ፣ ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረውንና በፍታ የለበሰውን ሰው፣ “እነዚህ አስደናቂ ነገሮች ሊፈጸሙ ምን ያህል ጊዜ ይቀራል?” አለው።
እነርሱም በታላቅ ድምፅ፣ “ሁሉን የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፤ እስከ መቼ አትፈርድም? እስከ መቼስ ደማችንን በምድር በሚኖሩት ላይ አትበቀልም?” አሉ።