በሰዎች የሚደርሰው ጣጣ አይደርስባቸውም፤ እንደ ማንኛውም ሰው መከራ አያገኛቸውም።
ክፉ ሰው በመቅሠፍት ቀን እንደሚጠበቅ፣ በቍጣም ቀን እንደሚተርፍ አታውቁምን?
ስለዚህ ነገር ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፤ ሰውነቴም በፍርሀት ይንቀጠቀጣል።
ቤታቸው ያለ ሥጋት በሰላም ይኖራል፤ የእግዚአብሔርም በትር የለባቸውም።
እንግዲህ፣ ክፉዎች ይህን ይመስላሉ፤ ሁልጊዜ ግድ የለሽና ሀብት በሀብት ናቸው።
ነገር ግን ጌታ በሚፈርድብን ጊዜ እንገሠጻለን፤ ይኸውም ከዓለም ጋራ ዐብረን እንዳንኰነን ነው።
ልጆች ሁሉ በሚቀጡበት ቅጣት ተካፋይ ካልሆናችሁ፣ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።
እኔ የምወድዳቸውን እገሥጻለሁ፤ እቀጣለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ።