እነሆ፤ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤ አንተ የሚያመነዝሩትን ሁሉ ታጠፋቸዋለህ።
ሳኦል ለእግዚአብሔር ስላልታመነ ሞተ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልጠበቀም፤ ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤
መርዶክዮስም የመልካም ምኞት መግለጫና ማረጋገጫ የሆነውን ደብዳቤ በጠረክሲስ ግዛት ውስጥ በሚገኙት አንድ መቶ ሃያ ሰባት አውራጃዎች ለሚኖሩት አይሁድ ሁሉ ላከ፤
በተግባራቸው ረከሱ፤ በድርጊታቸውም አመንዝሮች ሆኑ።
ሥርዐትህን ስለማይሹ፣ ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው።
“በምድሪቱ ከሚኖሩት ጋራ ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አምላኮቻቸውን ተከትለው ባመነዘሩና መሥዋዕትም ባቀረቡላቸው ጊዜ ይጋብዙሃል፤ አንተም መሥዋዕታቸውን ትበላለህ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፤ በከንፈሩም ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ የሚያመልከኝም፣ ሰው ባስተማረው ሰው ሠራሽ ሥርዐት ነው።
አንተ ተክለሃቸዋል፤ ሥርም ሰድደዋል፤ አድገዋል፤ ፍሬም አፍርተዋል። ሁልጊዜ አንተ በአፋቸው ላይ አለህ፤ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።
የእስራኤል ተስፋ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጥለውህ የሚሄዱ ሁሉ ያፍራሉ፤ ፊታቸውን ከአንተ የሚመልሱ በምድር ውስጥ ይጻፋሉ፤ የሕይወትን ውሃ ምንጭ፣ እግዚአብሔርን ትተዋልና።
ልባችሁ የተመኘውን፣ ዐይናችሁ ያየውን ሁሉ ተከትላችሁ እንዳታመነዝሩ እነዚህን ዘርፎች በማየት የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በማስታወስ እንድትታዘዙ ማስታወሻ ይሆኗችኋል።
አሁን ግን እናንተ ቀድሞ ርቃችሁ የነበራችሁ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም አማካይነት ቀርባችኋል።
መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁት ለእናንተ፣ ቀርበው ለነበሩትም ለእነርሱ ሰላምን ሰበከ፤
አመንዝሮች ሆይ፤ ከዓለም ጋራ ወዳጅነት ከእግዚአብሔር ጋራ ጠላትነት መሆኑን አታውቁምን? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኗል።