ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤ እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሯል!
እናገለግለው ዘንድ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ ማን ነው? ወደ እርሱ ብንጸልይስ ምን እናገኛለን?’
‘እግዚአብሔርን ለማስደሰት መሞከር፣ ለሰው አንዳች አይጠቅምም’ ብሏልና።
ደግሞ ‘ያገኘሁት ጥቅም ምንድን ነው? ኀጢአት ባለመሥራቴስ ምን አተረፍሁ?’ ብለህ ጠይቀኸዋል።
‘ማጕረምረሜን እረሳለሁ፤ ገጽታዬን ቀይሬ ፈገግ እላለሁ’ ብል፣
በደለኛ መሆኔ ካልቀረ፣ ለምን በከንቱ እለፋለሁ?
ልብሴ እንኳ እስኪጸየፈኝ ድረስ፣ በዐዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ።
ንጹሕ እጅና ቅን ልብ ያለው፤ ነፍሱን ለሐሰት ነገር የማያስገዛ፤ በውሸት የማይምል።
እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህንም እዞራለሁ፤
አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።
“እንዲህም ብላችኋል፤ ‘እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ እርሱ የሚፈልገውን ሁሉ በማድረግና በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ሐዘንተኞች ሆነን በመመላለስ ምን ተጠቀምን?
ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።