አምላክ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤ አምላኬ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን እንዲህ ርቀህ ቆምህ? በመከራ ጊዜስ ለምን ድምፅህን አጠፋህ?
እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈጥነህ መልስልኝ፤ መንፈሴ ደከመች፤ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልሆን፣ ፊትህን ከእኔ አትሰውር።
መከራ እየተቃረበ ነውና፣ የሚረዳኝም የለምና፣ ከእኔ አትራቅ።
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤ ዐጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን አይተሃልና ዝም አትበል፤ ጌታ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
ወደ እኔ ቀርበህ ታደገኝ፤ ስለ ጠላቶቼም ተቤዠኝ።
እኔ ግን ችግረኛና ድኻ ነኝ፤ አምላክ ሆይ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ አንተ ረዳቴና፣ ታዳጊዬም ነህና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አትዘግይ።