የቤትህ ቅናት በላችኝ፤ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ዐርፏል።
እርሱም፣ “እኔ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ እስራኤላውያን ኪዳንህን ትተዋል፤ መሠዊያዎችህን አፍርሰዋል፤ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና። የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፤ አሁንም እኔን ለመግደል ይፈልጋሉ” አለ።
ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር የተነሣ፣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ፣ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤
“ወንድሞቼን ከእኔ አርቋል፤ ከሚያውቁኝም ተገለልሁ።
ጠላቶቼ ቃልህን ዘንግተዋልና፣ ቅናት አሳረረኝ።
ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ሊያጠፉኝ ዛቱ፤ ቀኑንም ሙሉ ተንኰል ይሸርባሉ።
ዐላፊ አግዳሚው ሁሉ ዘረፈው፤ ለጎረቤቶቹ መዘባበቻ ሆነ።
ክርስቶስ ራሱን ደስ አላሠኘምና፤ ነገር ግን፣ “አንተን የሰደቡበት ስድብ በእኔ ላይ ደረሰብኝ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ሆነበት።