ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፤ ዕፍረትም ፊቴን ሸፍኗልና።
ውርደቴ ቀኑን ሙሉ በፊቴ ነው፤ ፊቴም ዕፍረትን ተከናንቧል።
ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቈጥረናል።
ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ ጢሜን ለሚነጩ ጕንጬን ሰጠሁ፤ ፊቴን ከውርደት፣ ከጥፋትም አልሰወርሁም።
በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣ የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣ የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ታውቃለህ፤ እንግዲህ ዐስበኝ፤ ጐብኘኝም፤ አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ። ታጋሽ እንደ መሆንህ አታጥፋኝ፤ ባንተ ምክንያት የሚደርስብኝን ነቀፋ ዐስብ።
ሄሮድስም ከወታደሮቹ ጋራ ናቀው፤ አፌዙበትም፤ የክብር ልብስ አልብሶም ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው።
የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።