ግርማው በእስራኤል ላይ፣ ኀይሉም ከደመናት በላይ ነው፣ እግዚአብሔርን ብርታት የአንተ ነው በሉት።
ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በታላቅ ጠፈሩ አመስግኑት።
የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው።
“አንተን ለመርዳት በሰማያት ላይ፣ በደመናትም ላይ በግርማው እንደሚገሠግሥ፣ እንደ ይሹሩን አምላክ ያለ ማንም የለም።
ዘላለማዊ አምላክ መኖሪያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከሥርህ ናቸው፤ ‘እርሱን አጥፋው!’ በማለት፣ ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል።
ምክንያቱም ከግርማዊው ክብር “በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው” የሚል ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርና ሞገስ ተቀብሏል፤
ደግሞም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ኀይለኛ ወራጅ ውሃ ድምፅ፣ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ የሚመስል እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን ቻይ ጌታ አምላካችን ነግሧልና።