አምላክ ሆይ፤ የክብር አካሄድህ ታየ፤ ይህም አምላኬና ንጉሤ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያደርገው የክብር አካሄድ ነው።
ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሆነው በቅኔና በበገና፣ በመሰንቆና በከበሮ፣ በጸናጽልና በመለከት በሙሉ ኀይላቸው በዓሉን በደስታ ያከብሩ ነበር።
ሰዎችም፣ “በርግጥ ለጻድቃን ብድራት ተቀምጦላቸዋል፤ በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ” ይላሉ።
ስለዚህ በመቅደስ ውስጥ አየሁህ፤ ኀይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ።