በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፤ በአንደበቴም አመሰገንሁት።
ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?
አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከታች አንሥተኸኛልና፣ ጠላቶቼም በላዬ እንዳይደሰቱ አድርገሃልና፣ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ ወደ ጌታም እንዲህ ብዬ ጮኽሁ፤
“በእኔ ወደ ጕድጓድ መውረድ፣ በመሞቴ ምን ጥቅም ይገኛል? ዐፈር ያመሰግንሃልን? ታማኝነትህንስ ይናገራልን?
ይህ ችግረኛ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።