ትልሟን በውሃ ታረሰርሳለህ፤ ቦይዋን ታስተካክላለህ፤ በካፊያ ታለሰልሳለህ፤ ቡቃያዋንም ትባርካለህ።
ሰዎችን ለመቅጣት ደመና ያመጣል፤ ወይም በዚሁ ምድሩን አጠጥቶ ፍቅሩን ይገልጻል።
ከላይ ከእልፍኝህ ተራሮችህን ታጠጣለህ፤ ምድርም በሥራህ ፍሬ ትረካለች።
ሰማይን በደመናት የሚሸፍን እርሱ ነው፤ ለምድርም ዝናብን ይሰጣል፤ በተራሮችም ላይ ሣር ያበቅላል።
መንጋህ መኖሪያው አደረጋት፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከበረከትህ ለድኾች ሰጠህ።
ዝናብን በወቅቱ እሰጣችኋለሁ፤ ምድሪቱ እህሏን፣ የሜዳ ዛፎችም ፍሬአቸውን ይሰጣሉ።
ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትውረድ፤ ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፣ ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ።