እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፋታቸው የተነሣ እንዳያመልጡ፣ ሕዝቦቹን በቍጣህ ጣላቸው።
ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁና እንደ ተጋደሙ፣ ቍልቍልም እንደ ተወረወሩና መነሣት እንደማይችሉ ተመልከት!
ክፉዎች ጻድቁን ይከታተሉታል፤ ሊገድሉትም ይሻሉ።
በሀብታቸው የሚመኩትን፣ በብልጽግናቸውም የሚታመኑትን ለምን እፈራለሁ?
ሞት ሳይታሰብ ድንገት ይምጣባቸው፤ በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ይውረዱ፤ ክፋት በመካከላቸው ዐድራለችና።
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
ጌታ ሆይ፤ ግፍንና ሁከትን በከተማዪቱ ውስጥ አይቼአለሁና፣ ግራ አጋባቸው፤ ቋንቋቸውንም ደበላልቅ።
እነርሱ ያለ በደሌ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተው መጡ፤ አንተ ግን ትረዳኝ ዘንድ ተነሥ፤ ሁኔታዬንም ተመልከት።
ሰው ነፋስን መቈጣጠር አይችልም፤ በዕለተ ሞቱም ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፤ በጦርነት ጊዜ ማንም ከግዴታ ነጻ እንደማይሆን፣ ክፋትም የሚለማመዷትን አትለቃቸውም።
እናንተ፣ “ከሞት ጋራ ቃል ኪዳን ገብተናል፤ ከሲኦልም ጋራ ስምምነት አድርገናል፤ ውሸትን መጠጊያችን፣ ሐሰትን መደበቂያችን አድርገናል፤ ታላቅ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣ ሊነካን አይችልም” በማለት ታብያችኋል።
ያዕቆብን አሟጥጠው ስለ በሉት፣ ፈጽመው ስለ ዋጡት፣ መኖሪያውንም ወና ስላደረጉ፣ በማያውቁህ ሕዝቦች፣ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ፣ ቍጣህን አፍስስ።
ስሜ ወደሚጠራበት ወደዚህ ቤት መጥታችሁ በፊቴ ትቆሙና “ደኅና ነን” እያላችሁ እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ታደርጋላችሁ።
ዐይኖችህ ክፉውን እንዳያዩ እጅግ ንጹሓን ናቸው፤ አንተ በደልን መመልከት አትችልም፤ ታዲያ፣ አታላዮችን ለምን ትመለከታለህ? ክፉው ከራሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠውስ፣ ለምን ዝም ትላለህ?