ጌታ ሆይ፤ ግፍንና ሁከትን በከተማዪቱ ውስጥ አይቼአለሁና፣ ግራ አጋባቸው፤ ቋንቋቸውንም ደበላልቅ።
በዚህ ጊዜ፣ “ከአቤሴሎም ጋራ ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ስለዚህ ዳዊት፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ብሎ ጸለየ።
በኢየሩሳሌም ባሉ ነቢያትም ላይ፣ የሚዘገንን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ፤ በመዋሸትም ይኖራሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ፣ የክፉዎችን እጅ ያበረታሉ፤ በእኔ ዘንድ ሁሉም እንደ ሰዶም፣ ነዋሪዎቿም እንደ ገሞራ ናቸው።”
የውሃ ጕድጓድ ውሃ እንደሚያመነጭ፣ እርሷም እንዲሁ ክፋቷን ታፈልቃለች። ዐመፅና ጥፋት በውስጧ ይስተጋባል፤ ሕመሟና ቍስሏ ዘወትር ይታየኛል።