እግዚአብሔር ሆይ፤ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤ በማለዳ ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ፤ ፈቃድህንም በጥሞና እጠባበቃለሁ።
የድኾች ልቅሶ ወደ እርሱ እንዲደርስ ሰበብ ሆኑ፤ የመከረኞችን ጩኸት ሰማ።
ትረዳኝ ዘንድ ጎሕ ሳይቀድድ ተነሥቼ እጮኻለሁ፤ ቃልህንም ተስፋ አደርጋለሁ።
ጌታ ሆይ፤ ድምፄን ስማ፤ ጆሮዎችህ የልመናዬን ቃል፣ የሚያዳምጡ ይሁኑ።
ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ አዎን፤ ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ ነፍሴ ጌታን ትጠባበቃለች።
አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ።
አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አልመለስህልኝም፤ በሌሊት እንኳ አላረፍሁም።
በአንተ ጠላቶቻችን በመጡበት እንዲመለሱ እናደርጋለን፤ በስምህም ባላጋራዎቻችንን ከእግራችን በታች እንረግጣለን።
በማታ፣ በጧትና በቀትር፣ እጮኻለሁ፤ እቃትታለሁም፤ እርሱም ድምፄን ይሰማል።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ በጎ ናትና ስማኝ፤ እንደ ርኅራኄም ብዛት መለስ በልልኝ።
አምላክ ሆይ፤ አንተ ከጥንት ጀምሮ ንጉሤ ነህ፤ በምድር ላይ ማዳንን አደረግህ።
ብፁዓን ናቸው፤ በቤትህ የሚኖሩ፣ እነርሱም ለዘላለም ያመሰግኑሃል። ሴላ
እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በጧትም ጸሎቴን በፊትህ አደርሳለሁ።
ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፤ መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሃለች። ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣ የዓለም ሕዝቦች ጽድቅን ይማራሉ።
ልመናዬን ሰምተሃል፤ “ርዳታም ፈልጌ ስጮኽ፣ ከመስማት ጆሮህን አትከልክል።”
ማለዳም ገና ጎሕ ሳይቀድድ፣ ኢየሱስ ተነሥቶ ከቤት ወጣ፤ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ ይጸልይ ጀመር።