አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤ ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት።
እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው፤
እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤ የጽድቅ ሥራም ይወድዳል፤ ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።
ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።
እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣ በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።
ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣ ከጓደኞችህ ይልቅ አንተን የደስታ ዘይት ቀባህ።
ፍትሕን የምትወድድ፣ ኀያል ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ትክክለኝነትን መሠረትህ፤ ፍትሕንና ቅንነትንም፣ ለያዕቆብ አደረግህ።
እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።
“ከፀሓይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ፣ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናል፤ በየስፍራውም ሁሉ ለስሜ ዕጣንና ንጹሕ ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናልና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“በመንጋው ውስጥ ተቀባይነት ያለው ተባዕት በግ ኖሮት ይህንኑ ሊሰጥ ተስሎ ሳለ፣ በማታለል ነውር ያለበትን እንስሳ ለጌታ የሚሠዋ ርጉም ይሁን፤ እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ ሊፈራ የሚገባ ነውና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የዚህን ሕግ ቃሎች በጥንቃቄ ባትከተልና አስደናቂና አስፈሪ የሆነውን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም ባታከብር፣
ከነዓናውያንና ሌሎቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ ይህን ሲሰሙ ይከብቡናል፤ ስማችንንም ከምድር ገጽ ያጠፉታል፤ እንግዲህ ስለ ታላቁ ስምህ ስትል የምታደርገው ምንድን ነው?”
ከዚያም ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆ አንድ ነጭ ፈረስ ነበረ፤ በፈረሱም ላይ፣ “ታማኝና እውነተኛ” የሚባል ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በጽድቅ ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።
ፍርዱ እውነትና ጽድቅ ነውና፤ በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን፣ ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባታል፤ ስለ ባሮቹም ደም ተበቅሏታል።”