አምላክ ሆይ፤ በጆሯችን ሰምተናል፤ አባቶቻችን በቀድሞ ዘመን፣ እነርሱ በነበሩበት ዘመን፣ ያደረግኸውን ነግረውናል።
ገና ላልተወለደ ሕዝብ፣ ጽድቁን ይነግራሉ፤ እርሱ ይህን አድርጓልና።
ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ፣ አምላክ ሆይ፤ ነፍሴም እንዲሁ አንተን ትናፍቃለች።
አምላክ ሆይ፤ ሳረጅና ስሸብትም አትተወኝ፤ ክንድህን ለመጪው ትውልድ፣ ኀይልህን ኋላ ለሚነሣ ሕዝብ ሁሉ፣ እስከምገልጽ ድረስ።
የድሮውን ዘመን አሰብሁ፤ የጥንቶቹን ዓመታት አውጠነጠንሁ።
እኔ ዛሬ እንደማደርገው፣ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል። ስለ አንተ ታማኝነትም፣ አባቶች ለልጆቻቸው ይነግራሉ።
ይህን ለልጆቻችሁ ተናገሩ፤ ልጆቻችሁ ለልጆቻቸው ይንገሩ፤ ልጆቻቸውም ለሚቀጥለው ትውልድ ይንገሩ።
በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፣ “አምላካችን እግዚአብሔር ያዘዛችሁ የምስክርነቶቹ፣ የሥርዐቶቹና የሕጎቹ ትርጕም ምንድን ነው?” ብሎ በሚጠይቅህ ጊዜ፣
ጌዴዎን መልሶ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ከሆነ ይህ ሁሉ እንዴት ሊደርስብን ቻለ? ‘እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር አውጥቶናል’ በማለት አባቶቻችን የነገሩን ታምራት የት አለ? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፤ በምድያማውያንም እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል” አለው።