ነፍሴ በውስጤ ተክዛለች፤ ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር፣ በአርሞንዔም ከፍታ፣ በሚዛር ተራራ ዐስብሃለሁ።
ስለዚህ ዳዊትና ዐብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ተነሥቶ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ሲነጋም ዮርዳኖስን ሳይሻገር የቀረ አንድም ሰው አልነበረም።
ዳዊት መሃናይም ሲደርስ፣ ከአሞናውያን ከተማ ከረባት የመጣው፣ የናዖስ ልጅ ሾቢ፣ ከሎደባር የመጣው የዓሚኤል ልጅ ማኪርና ከሮግሊም የመጣው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ
ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ፣ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን፣ ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዟልና።
አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳን፣ ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ?
እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ አቀናለሁ፤ ፍጹም ደስታዬ ወደ ሆነው አምላክ እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ በበገና አመሰግንሃለሁ።
ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤ አዳኜና አምላኬን፣ ገና አመሰግነዋለሁና።
ልቤ በዛለ ጊዜ፣ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ።
“ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች።
ጥቂት ዕልፍ ብሎ በግንባሩ በመደፋት፣ “አባቴ ሆይ፤ ቢቻል ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ፤ ነገር ግን እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን አንተ እንደምትፈልገው ይሁን” ብሎ ጸለየ።
በዘጠኝ ሰዓት ገደማ፣ ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ኤሎሄ! ኤሎሄ! ላማ ሰበቅታኒ?” እያለ ጮኸ፤ ትርጕሙም “አምላኬ፤ አምላኬ፤ ለምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።