ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ፣ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ፣ በነገር ጠዘጠዙኝ፣ ዐጥንቴም ደቀቀ።
ሰዎች ቀኑን ሙሉ፣ “አምላክህ የት አለ?” ባሉኝ ቍጥር፣ እንባዬ ቀንና ሌሊት፣ ምግብ ሆነኝ።
አምላክ ሆይ፤ አንተ ብርታቴ ነህና፣ ለምን ተውኸኝ? ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣ ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?
ልቤ በውስጤ ተጨነቀብኝ፤ የሞት ድንጋጤም በላዬ መጣ።
ግድ የለሽ ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤ የጠቢብ አንደበት ግን ፈውስን ያመጣል።
ስለ ምን ፈጽመህ ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረዥም ጊዜ ትተወናለህ?
በእግዚአብሔር ፊት የሚያገለግሉ ካህናት፣ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አደባባይ መካከል ሆነው ያልቅሱ፤ እንዲህም ይበሉ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አድን፤ ርስትህን በአሕዛብ መካከል መተረቻ፣ መሣቂያና መሣለቂያም አታድርግ፤ ለምንስ በሕዝቦች መካከል፣ ‘አምላካቸው ወዴት ነው?’ ይበሉን።”
ጠላቴም ታያለች፤ ኀፍረትንም ትከናነባለች፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ያለችኝን፣ ዐይኖቼ ውድቀቷን ያያሉ፤ አሁንም እንኳ፣ እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።
የብዙዎችም የልብ ሐሳብ የተገለጠ እንዲሆን፣ የአንቺም ነፍስ ደግሞ በሰይፍ ይወጋል።”