ልወድቅ ተቃርቤአለሁ፤ ከሥቃዬም ከቶ አልተላቀቅሁም።
እኔ ግን በጸናች ፍቅርህ እታመናለሁ፤ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
እነርሱ ግን እኔ ስሰናከል በእልልታ ተሰበሰቡ፤ ግፈኞች በድንገት ተሰበሰቡብኝ፤ ያለ ዕረፍትም ቦጫጨቁኝ።
ከምድር ተነሥተው ጠላቶቼ የሆኑት፣ በላዬ ደስ አይበላቸው፤ እንዲያው የሚጠሉኝ፣ በዐይናቸው አይጣቀሱብኝ።
ዐንገቴን ደፋሁ፤ ጐበጥሁም፤ ቀኑንም ሙሉ በትካዜ ተመላለስሁ።
ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ። ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤ መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ።