አምላኬ፣ ጌታዬ፤ ለእኔ ለመሟገት ተነሥ! ልትከራከርልኝም ተንቀሳቀስ።
ተሟገትልኝ፤ አድነኝም፤ እንደ ቃልህም ሕያው አድርገኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ።
ጌታ ሆይ፤ ንቃ! ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፤ ለዘላለምም አትጣለን።
ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? መከራችንንና መጠቃታችንን ለምን ትረሳለህ?
እነርሱ ያለ በደሌ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተው መጡ፤ አንተ ግን ትረዳኝ ዘንድ ተነሥ፤ ሁኔታዬንም ተመልከት።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤ በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤ አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!
የሕዝቦች ጉባኤ ይክበብህ፤ አንተም ከላይ ሆነህ ግዛቸው፤
ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ ጻድቅ አምላክ ሆይ፤ የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ ጻድቁን ግን አጽና።
አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ ለዐላማህ ተሟገት፤ ሞኝ ሰው ቀኑን ሙሉ እንደሚያላግጥብህ ዐስብ።
በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ደምቀህ ታይ። ኀይልህን አንቀሳቅስ፤ መጥተህም አድነን።
እርሱም፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤ አምላኬና መዳኛ ዐለቴም ነህ’ ብሎ ይጠራኛል።
የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፤ ተነሥ፤ ተነሥ! ኀይልን ልበስ፤ እንዳለፉት ዘመናት፣ በጥንት ትውልዶችም እንደ ሆነው ሁሉ ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ፣ ታላቁን ዘንዶ የወጋህ አንተ አይደለህምን?
እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኔ ላይ የተደረገውን ግፍ አየህ፤ ፍርዴን ፍረድልኝ!
ቶማስም፣ “ጌታዬ፤ አምላኬም!” አለው።