እግዚአብሔር የባሪያዎቹን ነፍስ ይቤዣል፤ እርሱንም መጠጊያ ያደረገ አይፈረድበትም።
ከጕዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይሥሐቅ ስም ይጠሩ፤ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።”
ዳዊትም ለብኤሮታዊው ለሬሞን ልጆች ለሬካብና ለወንድሙ ለበዓና እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን፣
ከዚያም ንጉሡ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳናት ሕያው እግዚአብሔርን!
ሕይወትሽን ከጥፋት ጕድጓድ የሚያድን፣ ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣
እርሱም እስራኤልን፣ ከኀጢአቱ ሁሉ ያድነዋል።
መንፈሴን በእጅህ እሰጣለሁ፤ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ ሆይ፤ አንተ ተቤዠኝ።
ክፉዎች በጻድቃን ላይ ያሤራሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል።
ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤ ቀስታቸውም ይሰበራል።
ዝማሬ በማቀርብልህ ጊዜ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ፤ አንተ የተቤዠሃትም ነፍሴ እልል ትላለች።
ጌታ ሆይ፤ ለእኔ ተሟገትኽልኝ፤ ሕይወቴንም ተቤዠህ።
እናንተም በመጨረሻው ዘመን ሊገለጥ የተዘጋጀው ድነት እስኪመጣ ድረስ በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል።
እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ “መጽሐፉን ልትወስድ፣ ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል።