እርሱ ተናግሯልና ሆኑ፤ አዝዟልና ጸኑም።
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።
እግዚአብሔርም “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።
በእግዚአብሔር ቃል ሰማያት ተሠሩ፤ በአፉም እስትንፋስ የከዋክብት ሰራዊት።
ምስክርነትህ የጸና ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ ዘላለሙ፣ ቤትህ በቅድስና ይዋባል።
ጌታ ካላዘዘ በቀር፣ ተናግሮ መፈጸም የሚችል ማን ነው?
እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዟል። የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።
ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠሩ በእምነት እንረዳለን፤ ስለዚህ የሚታየው ነገር የተፈጠረው ከሚታየው እንዳልሆነ እንገነዘባለን።
“ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤ ክብርና ሞገስ፣ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና፤ በፈቃድህም ተፈጥረዋልና፤ ሆነዋልምና።”