አንተ መጠጊያዬ ነህና፣ በስውር ከተዘረጋብኝ ወጥመድ አውጣኝ።
ነፍሳችን እንደ ወፍ፣ ከዐዳኝ ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመዱ ተሰበረ፤ እኛም አመለጥን።
ትዕቢተኞች ወጥመድ በስውር አስቀመጡብኝ፤ የመረባቸውን ገመድ ዘረጉብኝ፤ በመንገዴም ላይ አሽክላ አኖሩ። ሴላ
ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
ዐለቴና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣ በፊትህ ያማረ ይሁን።
ነፍሴንም ይመልሳታል። ስለ ስሙም፣ በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።
ዐይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው፤ እግሮቼን ከወጥመድ የሚያላቅቃቸው እርሱ ነውና።
ያለ ምክንያት ወጥመዳቸውን በስውር አስቀምጠውብኛልና፤ ያለ ምክንያት ለነፍሴ ጕድጓድ ቈፍረውላታል።
ለእግሬ ወጥመድን ዘረጉ፤ ነፍሴንም አጐበጧት፤ በመተላለፊያዬ ላይ ጕድጓድ ቈፈሩ፤ ነገር ግን ራሳቸው ገቡበት። ሴላ
ባልንጀራውን የሚሸነግል፣ ለገዛ እግሩ መረብ ይዘረጋል።
እርሱ ግን፣ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ ፍጹም የሚሆነው በድካም ጊዜ ነውና” አለኝ። ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ያድር ዘንድ፣ ይበልጥ ደስ እያለኝ በድካሜ እመካለሁ።
ይኸውም ወደ አእምሯቸው ይመለሳሉ፤ ፈቃዱን ሊያስፈጽማቸው ምርኮኛ አድርጎ ከያዛቸው ከዲያብሎስ ወጥመድም ያመልጣሉ በማለት ነው።