እግዚአብሔር በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጧል፤ እግዚአብሔር በንጉሥነቱ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
እኔም ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸውን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ለማጥፋት እነሆ፤ በምድር ላይ የጥፋት ውሃ አወርዳለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሁሉ ይጠፋል።
ለዝናብ መውረጃን፣ ለመብረቅም መንገድን ያበጀ ማን ነው?
እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ንጉሥ ነው፤ ሕዝቦችም ከምድሩ ይጠፋሉ።
የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤ እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ።
አንተ የባሕሮችን ማስገምገም፣ የማዕበላቸውን ፉጨት፣ የሕዝቦችንም ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ።
ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል።
እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤ ብርታትንም ታጠቀ፤ ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ ማንም አይነቀንቃትም።
እግዚአብሔር ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን ተቀምጧል፤ ምድር ትናወጥ።
“በእነዚያ ነገሥታት ዘመን፣ የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይፈርስና ለሌላም ሕዝብ የማይሰጥ መንግሥት ይመሠርታል፤ እነዚያን መንግሥታት ሁሉ ያደቅቃል፤ እስከ መጨረሻውም ያጠፋቸዋል፤ ይህ መንግሥት ራሱ ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉው አድነን እንጂ፤ መንግሥት፣ ኀይል፣ ክብርም ለዘላለሙ ያንተ ነውና፤ አሜን። ’
እነርሱም በፍርሀት ተውጠው እርስ በርሳቸው፣ “ነፋሱም ሞገዱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።
እንግዲህ ዘላለማዊ ለሆነው፣ ለማይሞተው፣ ለማይታየውና ብቻውን አምላክ ለሆነው ንጉሥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን።