የልጅነቴን ኀጢአት፣ መተላለፌንም አታስብብኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ ብዛት፣ እንደ ምሕረትህም መጠን አስበኝ።
መራራ ነገር ትጽፍብኛለህ፤ የወጣትነቴንም ኀጢአት ታወርሰኛለህ።
ዐጥንቱን የሞላው የወጣትነት ብርታት፣ ከርሱ ጋራ በዐፈር ውስጥ ይተኛል።
ብፁዓን ናቸው፤ ፍትሕ እንዳይዛነፍ የሚጠብቁ፣ ጽድቅን ሁልጊዜ የሚያደርጉ፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ ለሕዝብህ ሞገስ ስታድል ዐስበኝ፤ በምታድናቸውም ጊዜ ርዳኝ፤
የአባቶቹ በደል በእግዚአብሔር ፊት ይታሰብ፤ የእናቱም ኀጢአት አይደምሰስ።
ድኻውንና ችግረኛውን፣ ልቡም የቈሰለውን፣ እስከ ሞት አሳደደ እንጂ፣ ምሕረት ያደርግ ዘንድ አላሰበምና።
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ርዳኝ፤ እንደ ምሕረትህም አድነኝ።
ለባሪያህ እንደ ምሕረትህ መጠን አድርግ፤ ሥርዐትህንም አስተምረኝ።
ፊትህን በአገልጋይህ ላይ አብራ፤ በምሕረትህም አድነኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ መጠን፣ ምሕረት አድርግልኝ፤ እንደ ርኅራኄህም ብዛት፣ መተላለፌን ደምስስ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤
የአባቶቻችንን ኀጢአት በእኛ ላይ አትቍጠርብን፤ ምሕረትህ ፈጥና ወደ እኛ ትምጣ፤ በጭንቅ ላይ እንገኛለንና።
እነሆ፤ በሥቃይ የተጨነቅሁት፣ ለጥቅሜ ሆነ፤ ከጥፋት ጕድጓድ፣ በፍቅርህ ጠበቅኸኝ፤ ኀጢአቴንም ሁሉ፣ ወደ ኋላህ ጣልህ።
“ስለ ራሴ ስል መተላለፍህን የምደመስስልህ፣ እኔ፣ እኔው ነኝ፤ ኀጢአትህን አላስባትም።
ስለ ራሴ፣ ስለ ራሴ ስል አደርጋለሁ፤ ራሴን ለውርደት እንዴት አሳልፌ እሰጣለሁ? ክብሬን ለማንም አልሰጥም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከልክ በላይ አትቈጣን፤ ኀጢአታችንንም ለዘላለም አታስብ፤ እባክህ ተለመነን፤ ፊትህን ወደ እኛ መልስ፤ ሁላችንም የአንተ ሕዝብ ነንና።
እንግዲህ ዕፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤ ውርደታችንም ይሸፍነን፤ እኛም አባቶቻችንም፣ እግዚአብሔር አምላካችንን በድለናልና፤ ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን አልታዘዝንም።”
ከእንግዲህ ማንም ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም ወንድሙን፣ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤ ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ፣ ሁሉም እኔን ያውቁኛልና፤” ይላል እግዚአብሔር። “በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስብም።”
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ያን ሰው በቤተ መቅደስ አግኝቶ፣ “እነሆ፣ ተፈውሰሃል፤ ከእንግዲህ ግን ኀጢአት አትሥራ፤ አለዚያ ከዚህ የባሰ ይደርስብሃል” አለው።
በዚያም ለሠላሳ ስምንት ዓመት ሕመምተኛ ሆኖ የኖረ አንድ ሰው ነበር።
በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውን ከእንግዲህ አላስብም።”