አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣ ከቶ አያፍሩም፤ ነገር ግን እንዲያው ያለ ምክንያት፣ ተንኰለኞች የሆኑ ያፍራሉ።
“ዛብሎን፣ በባሕር ዳር ይኖራል፤ የመርከቦች መጠጊያም ይሆናል፤ ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል።
ሳኦል ለእግዚአብሔር ስላልታመነ ሞተ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልጠበቀም፤ ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤
በጥላቻ ቃል ከብበውኛል፤ ያለ ምክንያትም ጥቃት አድርሰውብኛል።
እብሪተኞች ያለ ምክንያት በደል አድርሰውብኛልና ይፈሩ፤ እኔ ግን ትእዛዞችህን አሰላስላለሁ።
የባሪያዎች ዐይን ወደ ጌታቸው እጅ፣ የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት፣ ምሕረት እስከሚያደርግልን ድረስ፣ የእኛም ዐይኖች ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለከታሉ።
ጠላቶቹን ኀፍረት አከናንባቸዋለሁ፤ እርሱ ግን በራሱ ላይ የደፋው ዘውድ ያበራል።”
እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤ ሰው ያላገጠብኝ፣ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ።
እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ አይዞህ፣ በርታ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁና አልፈር፤ ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ ሲኦል ገብተውም ጸጥ ይበሉ።
በጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩ፣ ትዕቢትንና ንቀትን የተሞሉ፣ ዋሾ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።
ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርጋለች፤ እርሱ ረዳታችንና ጋሻችን ነው።
በጭንቀቴ ደስ የሚላቸው፣ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ ዕፍረትንና ውርደትን ይከናነቡ።
እግዚአብሔርን ደጅ ጥና፤ መንገዱንም ጠብቅ፤ ምድሪቱን ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ።
ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤ እጅግም ይደነግጣሉ፤ በመጡበት ይመለሳሉ፤ ድንገትም ይዋረዳሉ።
ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ድነቴም የሚመጣልኝ ከርሱ ዘንድ ነው።
ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤ ተስፋዬ ከርሱ ዘንድ ነውና።
ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ፣ ከራሴ ጠጕር በዙ፤ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልጉ፣ በከንቱም የሚጠሉኝ ብዙዎች ሆኑ፤ ያልሰረቅሁትን ነገር፣ መልሰህ አምጣ ተባልሁ።
ጌታ እግዚአብሔር የሰራዊት ጌታ ሆይ፤ አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣ በእኔ ምክንያት አይፈሩ፤ የእስራኤል አምላክ ሆይ፤ አንተን አጥብቀው የሚሹ፣ ከእኔ የተነሣ አይዋረዱ።
ባላንጣ የሆኑብኝ ይፈሩ፤ ይጥፉም፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ፣ ንቀትንና ውርደትን ይከናነቡ።
በዚያ ቀን እንዲህ ይባላል፤ “እነሆ፤ አምላካችን ይህ ነው፤ በርሱ ታመንን፤ እርሱም አዳነን፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ በርሱ ታመንን፤ በማዳኑም ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ።”
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።
ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ፣ እቴጌዎቻቸው ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽን ትቢያ ይልሳሉ፤ አንቺም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔን ተስፋ የሚያደርጉም አያፍሩም።”
ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋራ ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤ ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤ ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም።
እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው።
እኔ ግን እግዚአብሔርን ተስፋ አደርጋለሁ፤ የድነቴን አምላክ እጠብቃለሁ፤ አምላኬ ይሰማኛል።
ይህም፣ ‘ያለ ምክንያት ጠሉኝ’ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው።
ነገር ግን ገና ያላየነውን ተስፋ ብናደርግ፣ በትዕግሥት እንጠብቀዋለን።