ዐይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው፤ እግሮቼን ከወጥመድ የሚያላቅቃቸው እርሱ ነውና።
ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ከአንተ ቀጥሎ በጌታዬ በንጉሡ ዙፋን ላይ ማን መቀመጥ እንዳለበት እንድታሳውቀው የእስራኤል ዐይን ሁሉ አንተን ይመለከታል።
አምላካችን ሆይ፤ አንተ አትፈርድባቸውምን? የመጣብንን ይህን ታላቅ ሰራዊት እንቋቋም ዘንድ ዐቅም የለንምና የምናደርገውን አናውቅም፤ ነገር ግን ዐይኖቻችን ወዳንተ ናቸው።”
የባሪያዎች ዐይን ወደ ጌታቸው እጅ፣ የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት፣ ምሕረት እስከሚያደርግልን ድረስ፣ የእኛም ዐይኖች ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለከታሉ።
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ፤ መጠጊያዬም አንተ ነህ፤ እንግዲህ ነፍሴን አትተዋት።
አንተ መጠጊያዬ ነህና፣ በስውር ከተዘረጋብኝ ወጥመድ አውጣኝ።
“በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና፤ ወፍ እንደሚያጠምዱ ሰዎች፣ ወጥመድ ዘርግተው ሰው እንደሚይዙ ሰዎችም ያደባሉ።