አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አልመለስህልኝም፤ በሌሊት እንኳ አላረፍሁም።
ሰዎች ቀኑን ሙሉ፣ “አምላክህ የት አለ?” ባሉኝ ቍጥር፣ እንባዬ ቀንና ሌሊት፣ ምግብ ሆነኝ።
የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕዝብህ ጸሎት ላይ ቍጣህ የሚነድደው፣ እስከ መቼ ድረስ ነው?
አዳኜ የሆንህ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በቀንና በሌሊት በፊትህ እጮኻለሁ።
ጸሎት እንዳያልፍ፣ ራስህን በደመና ሸፈንህ።
ርዳታ ፈልጌ ብጣራና ብጮኽ እንኳ፣ ጸሎቴን መስማት አልፈለገም።
ትቷቸውም እንደ ገና በመሄድ ለሦስተኛ ጊዜ ቀደም ብሎ የጸለየውን ጸሎት ደገመ።
እግዚአብሔርስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? ከመጠን በላይስ ችላ ይላቸዋልን?
ከእነዚያም ቀናት በአንዱ ኢየሱስም ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጥቶ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ዐደረ።
እንደ ገና ልናያችሁና በእምነታችሁ የጐደለውን ለማሟላት ሌሊትና ቀን እጅግ ተግተን እንጸልያለን።
ሳላቋርጥ ሌሊትና ቀን በጸሎቴ ስለ አንተ ሳስብ፣ ቀደምት አባቶች እንዳደረጉት በንጹሕ ኅሊና የማመልከውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።