አሳድደው ደረሱብኝ፤ ከበቡኝም፤ መሬት ላይ ሊዘርሩኝም አፈጠጡብኝ።
ችግረኞችንና ድኾችን ለመጣል፣ አካሄዳቸው ቀና የሆነውንም ለመግደል፣ ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፤ ቀስታቸውንም ገተሩ።
ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ፤ በአንድነትም ዙሪያዬን ዐጥረው ያዙኝ።
ሳኦል በተራራው በአንዱ በኩል ሆኖ ሲያሳድድ፣ ዳዊትና ሰዎቹ ደግሞ በተራራው በሌላ በኩል ከሳኦል ለማምለጥ ይጣደፉ ነበር። ሳኦልና ወታደሮቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ከብበው ለመያዝ ተቃርበው ሳሉ፣