እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን አስነሥቷል፤ ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣ እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ፣ ለእስራኤል ልጆች። ሃሌ ሉያ።
በልግስና ለድኾች ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል፤ ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍጥረትህ ሁሉ ያመሰግንሃል፤ ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።
ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው። ለቅዱሳኑም ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ።
የክፉዎችን ሁሉ ቀንድ እሰብራለሁ፤ የጻድቃን ቀንድ ግን ከፍ ከፍ ይላል።
አንተ የብርታታቸው ክብር ነህና፤ በሞገስህም ቀንዳችንን ከፍ ከፍ አደረግህ።
ጋሻችን የእግዚአብሔር ነውና፤ ንጉሣችንም የራሱ የእስራኤል ቅዱስ ነው።
የእኔን ቀንድ ግን እንደ አውራሪስ ቀንድ ከፍ ከፍ አደረግኸው፤ በለጋ ዘይትም አረሰረስኸኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈውሰኝ፤ እፈወሳለሁ፤ አድነኝ እኔም እድናለሁ፤ አንተ ምስጋናዬ ነህና።
ገዦችን ከዙፋናቸው አውርዷቸዋል፤ ትሑታንን ግን ከፍ ከፍ አድርጓቸዋል፤
ይህም ለአሕዛብ መገለጥን የሚሰጥ ብርሃን፣ ለሕዝብህ ለእስራኤልም ክብር ነው።”
አሁን ግን እናንተ ቀድሞ ርቃችሁ የነበራችሁ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም አማካይነት ቀርባችኋል።
መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁት ለእናንተ፣ ቀርበው ለነበሩትም ለእነርሱ ሰላምን ሰበከ፤
ከዚህ የተነሣ እናንተ ከቅዱሳን ጋራ የአንድ አገር ዜጋ፣ የእግዚአብሔርም ቤተ ሰብ አባል ናችሁ እንጂ፣ ከእንግዲህ ወዲህ መጻተኞችና እንግዶች አይደላችሁም።
እርሱ ውዳሴህ ነው፤ በገዛ ዐይኖችህ ያየሃቸውን፣ እነዚያን ታላላቅና አስፈሪ ነገሮች ያደረገልህ አምላክህ ነው።
በምንጠራው ጊዜ ሁሉ አምላካችን እግዚአብሔር ለእኛ ቅርብ እንደ ሆነ አማልክቱ የሚቀርቡት ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማነው?
እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ የተቀደሰ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ገንዘቡ ያደረገው ሕዝብ ናችሁ።
ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፤ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ይለኛልና።