እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መሰወሪያ አድርጌአለሁና፣ ከጠላቶቼ አድነኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ።
ስምህን አመሰግን ዘንድ፣ ነፍሴን ከእስር አውጣት፤ ከምታደርግልኝም በጎ ነገር የተነሣ፣ ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።
ዘመኔ ያለው በእጅህ ነው፤ ከጠላቶቼ እጅ ታደገኝ፤ ከሚያሳድዱኝም አድነኝ።
ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን፣ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ በዚህም፣ አምላክ ከጐኔ መቆሙን ዐውቃለሁ።
ለእኔ ያሰበውን ወደሚፈጽምልኝ አምላክ፣ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጮኻለሁ።
አምላክ ሆይ፤ ከጠላቶቼ እጅ አድነኝ፤ ሊያጠቁኝ ከሚነሡብኝም ጠብቀኝ።
የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል።
እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጓል።