እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ልመናዬን አድምጥ፤ በታማኝነትህና በጽድቅህም፣ ሰምተህ መልስልኝ።
“አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ለባሪያህና ለቤቱ የሰጠኸውን ተስፋ ለዘላለም የጸና ይሁን፤ እንደተናገርኸውም ፈጽም፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ “አንተ አምላኬ ነህ” እልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የልመና ጩኸቴን ስማ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅንነት የቀረበውን አቤቱታዬን ስማ፤ ጩኸቴንም ስማ፤ ከአታላይ ከንፈር ያልወጣውን፣ ጸሎቴን አድምጥ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መጠጊያ አደረግሁ፤ ከቶም አልፈር፤ በጽድቅህም ታደገኝ።
በጽድቅህም ታደገኝ፤ አስጥለኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ አድነኝም።
ጌታ ሆይ፤ ቀድሞ እንዳደረግኸው የጽድቅ ሥራህ ሁሉ፣ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም፣ ከቅዱሱም ተራራህ ቍጣህን መልስ፤ በእኛ ኀጢአትና በአባቶቻችን በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ባሉት ዘንድ መሣለቂያ ሆነዋል።
ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።