እጅግ ተስፋ ቈርጫለሁና፣ ጩኸቴን ስማ፤ ከዐቅም በላይ ሆነውብኛልና፣ ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
እግዚአብሔር አላዋቂዎችን ይጠብቃል፤ እጅግ ተቸግሬ ሳለሁ አዳነኝ።
በውርደታችን ጊዜ ያሰበን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
ጠላት እስከ ሞት አሳድዶኛል፤ ሕይወቴንም አድቅቆ ከዐፈር ቀላቅሏል፤ ቀደም ብለው እንደ ሞቱትም፣ በጨለማ ውስጥ አኑሮኛል።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈጥነህ መልስልኝ፤ መንፈሴ ደከመች፤ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልሆን፣ ፊትህን ከእኔ አትሰውር።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅንነት የቀረበውን አቤቱታዬን ስማ፤ ጩኸቴንም ስማ፤ ከአታላይ ከንፈር ያልወጣውን፣ ጸሎቴን አድምጥ።
ከብርቱ ጠላቶቼ አዳነኝ፤ ከሚበረቱብኝ ባላጋሮቼም ታደገኝ።
የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር እንደማይ ሙሉ እምነቴ ነው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ! ስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ!
ብርቱዎች ጠላቶቼ ብዙ ናቸው፤ ያለ ምክንያት የሚጠሉኝም ስፍር ቍጥር የላቸውም።
ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ እንኳ፣ ተራሮችም ወደ ባሕር ጥልቅ ቢሰምጡ አንፈራም።
እነሆ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጨካኞች ያለ በደሌ፣ ያለ ኀጢአቴ በላዬ ተሰብስበው ዶለቱብኝ።
የአባቶቻችንን ኀጢአት በእኛ ላይ አትቍጠርብን፤ ምሕረትህ ፈጥና ወደ እኛ ትምጣ፤ በጭንቅ ላይ እንገኛለንና።
እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።
እግዚአብሔር የመረጣቸውን የሚከስስ ማን ነው? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፤
ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
“የእስራኤል ንጉሥ የወጣው በማን ላይ ነው? አንተስ የምታሳድደው ማንን ነው? የሞተ ውሻን? ወይስ ቍንጫ?