ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ፤ ችግሬንም በፊቱ እናገራለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ዐለቴ ሆይ፤ ሰምተህ እንዳልሰማ አትሁንብኝ፤ አንተ ዝም ካልኸኝ፤ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ እሆናለሁ።
ነፍሴ በውስጤ እየፈሰሰች፣ እነዚህን ነገሮች አስታወስሁኝ፤ ታላቅ ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ቤት እየመራሁ፣ በእልልታና በምስጋና መዝሙር፣ በአእላፍ ሕዝብ መካከል፣ እንዴት ከሕዝቡ ጋራ እሄድ እንደ ነበር ትዝ አለኝ።
ሰዎች ሆይ፤ ሁልጊዜ በርሱ ታመኑ፤ ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ
እግዚአብሔር ሆይ፤ በተጨነቁ ጊዜ ወደ አንተ መጡ፤ በገሠጽሃቸውም ጊዜ፣ በለኆሳስ ድምፅ ይጸልያሉ።
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ያግዘናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅም፤ መንፈስ ግን በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ይማልድልናል።
ኢየሱስ በዚህ ምድር በኖረበት ዘመን ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ልመናን ከታላቅ ጩኸትና ከእንባ ጋራ አቀረበ፤ ፍጹም ትሑት ሆኖ በመታዘዙም ጸሎቱ ተሰማለት።