እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤ ከዐመፀኞችም ሰዎች ጠብቀኝ፤
ምላሰኛ በምድሪቱ ጸንቶ አይኑር፤ ዐመፀኛውን ሰው ክፋት አሳድዶ ያጥፋው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፤ እግሮቼንም ለመጥለፍ ከሚያደቡ ዐመፀኞች ሰውረኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥተህ ግጠማቸውና ጣላቸው፤ በሰይፍህም ከክፉዎች ታደገኝ።
ከጠላቶቼም የሚታደገኝ እርሱ ነው። አንተ ከባላንጦቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኞች አዳንኸኝ።
አምላክ ሆይ፤ ፍረድልኝ፤ ካልታመኑህ ሕዝብ ጋራ ተሟገትልኝ፤ ከአታላዮችና ከክፉዎች ሰዎችም አድነኝ።
አምላኬ ሆይ፤ ከክፉ እጅ፣ ከግፈኛና ከጨካኝ መዳፍ አውጣኝ።