ለካህናቷ ድነትን አለብሳለሁ፤ ቅዱሳኗም በደስታ ይዘምራሉ።
“አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ተነሥ፣ ከኀይልህ ታቦት ጋራ ወደ ማረፊያ ቦታህ ግባ። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ካህናትህ ድነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በቸርነትህ ደስ ይበላቸው።
ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም እልል ይበሉ።”
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፤ እግሮቼንም ለመጥለፍ ከሚያደቡ ዐመፀኞች ሰውረኝ።
በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፤ ነፍሴ በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች፤ ሙሽራ ራሱን እንደሚያሳምር፣ ሙሽራዪቱም በዕንቈቿ እንደምታጌጥ፣ የድነትን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
ኤፍሬም በሐሰት፣ የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፤ ይሁዳ ለአምላክ የማይገዛ፣ የታመነውን ቅዱሱን የሚቃወም ነው።
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣ በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል።
እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ለምኑ ትቀበላላችሁ፤ ደስታችሁም ሙሉ ይሆናል።
ከክርስቶስ ጋራ አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁላችሁ ክርስቶስን ለብሳችሁታልና።