እግዚአብሔር ሆይ፤ ዳዊትን፣ የታገሠውንም መከራ ሁሉ ዐስብ።
እግዚአብሔር ኖኅንና በመርከቧ ውስጥ ከርሱ ጋራ የነበሩትን የዱርና የቤት እንስሳት ሁሉ ዐሰበ፤ በምድር ላይ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም ጐደለ።
በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ።
ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል?
“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ” ባሉኝ ጊዜ፣ ደስ አለኝ።
በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጥህ ሆይ፤ ዐይኖቼን ወደ አንተ አነሣለሁ።
እስራኤል እንዲህ ይበል፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ባይሆን ኖሮ፣
በእግዚአብሔር የሚታመኑ፣ ሳትናወጥ ለዘላለም እንደምትኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።
እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም።
እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣ በመንገዱም የሚሄዱ፤
እስራኤል እንዲህ ይበል፦ “ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጥልቅ ወደ አንተ እጮኻለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤ ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤ ሐሳቤ ለዐጕል ትልቅነት አልተነሣሣም፤ ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም።
ጭንቀቴንና መከራዬን ተመልከት፤ ኀጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
እግዚአብሔርም የጩኸታቸውን ሲቃ ሰማ፤ ከአብርሃም፣ ከይሥሐቅና ከያዕቆብ ጋራ የገባውንም ቃል ኪዳን ዐሰበ።
የጭንቀቴንና የመንከራተቴን፣ ምሬትንና ሐሞትን ዐስባለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኛ ላይ የደረሰውን ዐስብ፤ ውርደታችንን እይ፤ ተመልከትም።