ትልቅ ምርኮ እንዳገኘ ሰው፣ በቃልህ ደስ አለኝ።
ምስክርነትህ የዘላለም ውርሴ ናት፤ ልቤ በዚህ ሐሤት ያደርጋልና።
ሰው በሀብቱ ብዛት ደስ እንደሚለው፣ ምስክርነትህን በመከተል ደስ ይለኛል።
ከአእላፋት ብርና ወርቅ ይልቅ፣ ከአፍህ የሚወጣው ሕግ ይሻለኛል።
በተዋረደ መንፈስ ከተጨቈኑት ጋራ መሆን፣ ከትዕቢተኞች ጋራ ብዝበዛን ከመካፈል ይሻላል።
ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
ቃልህ በተገኘ ጊዜ በላሁት፤ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ ተጠርቻለሁና፣ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነልኝ።
ዳዊትን ወደ ታች መርቶ ባደረሰው ጊዜም፣ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያንና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሣ በየቦታው ተበታትነው ይበሉ፣ ይጠጡና ይዘፍኑ፣ ይጨፍሩም ነበር።