ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ዘለሉ።
ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የተራሮችም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቈጥቷልና ተንቀጠቀጡ።
ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣ ሢርዮንንም እንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል።
“ሰው የጥላ ውልብታ ነው፤ በከንቱም ይታወካል፤ ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል።
እናንተ ባለብዙ ጫፍ ተራሮች ሆይ፤ እግዚአብሔር ሊኖርበት የመረጠውን ተራራ፣ በርግጥ እግዚአብሔር ለዘላለም የሚኖርበትን ተራራ ለምን በቅናት ዐይን ታያላችሁ?
የሲና ተራራ እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት በጢስ ተሸፍኖ ነበር። ጢሱ ከምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ወደ ላይ ተትጐለጐለ፤ ተራራውም በሙሉ በኀይል ተናወጠ።
ሕዝቡም መብረቁንና ነጐድጓዱን የተራራውን መጤስና የመለከቱን ድምፅ ባዩና በሰሙ ጊዜ በፍርሀት ተንቀጠቀጡ፤ በርቀትም ቆሙ፤
ተራሮች በፊቱ ታወኩ፤ ኰረብቶችም ቀለጡ። ምድር በፊቱ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖሩት ሁሉ ተናወጡ።
ቆመ፤ ምድርን አንቀጠቀጠ፤ ተመለከተ፤ ሕዝቦችን አብረከረከ፤ የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ፤ የጥንት ኰረብቶችም ፈራረሱ፤ መንገዱ ዘላለማዊ ነው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በወንዞች ላይ ተቈጣህን? መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን? በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሠረገሎችህ በጋለብህ ጊዜ፣ በባሕር ላይ ተቈጥተህ ነበርን?
ከዚህ በኋላ ታላቅ ነጭ ዙፋንና በርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ። ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።