እግዚአብሔርን በአንደበቴ እጅግ አመሰግናለሁ፤ በታላቅ ሕዝብም መካከል አወድሰዋለሁ።
በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፤ በሽማግሌዎችም ሸንጎ ይወድሱት።
ሃሌ ሉያ። በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣ ለእግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ።
በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ “በአማልክት” ፊት በመዝሙር አወድስሃለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፍህን ቃል በሰሙ ጊዜ፣ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመስግኑህ።
በታላቅ ጉባኤ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበትም አወድስሃለሁ።
ስለ ጽድቁ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀርባለሁ፤ የልዑል እግዚአብሔርን ስም በመዝሙር አወድሳለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስለ ድንቅ ሥራዎችህም ሁሉ እናገራለሁ።
እንዲህም ይላል፤ “ስምህን ለወንድሞቼ ዐውጃለሁ፤ በጉባኤም መካከል አወድስሃለሁ።”