ከጾም የተነሣ ጕልበቴ ዛለ፤ ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ ለበሰ።
ቈዳና ዐጥንት ብቻ ሆኜ ቀረሁ፤ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።
እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤ በውስጤም ቀለጠ።
ነፍሴን በጾም ባስመረርሁ ጊዜ፣ እነርሱ ሰደቡኝ።
ማቅ በለበስሁ ጊዜ፣ መተረቻ አደረጉኝ።
አርባ ቀን እና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ።
ብዙ ጥሬአለሁ፤ ብዙ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤ ተርቤአለሁ፤ ተጠምቻለሁ፤ ብዙ ጊዜ ምግብ ሳልቀምስ ኖሬአለሁ፤ በብርድና በዕራቍትነት ተቈራምጃለሁ።
ስለዚህ የዛለውን ክንዳችሁንና የደከመውን ጕልበታችሁን አበርቱ።