ምድረ በዳውን ወደ ውሃ መከማቻ፣ ደረቁንም ምድር ወደ ውሃ ምንጭ ቀየረ።
ባድማውንና በረሓውን መሬት የሚያጠግብ፣ ሣርም እንዲበቅልበት የሚያደርግ ማን ነው?
እርሱ ዐለቱን ወደ ኵሬ፣ ቋጥኙንም ወደ ውሃ ምንጭ ለወጠ።
ምንጭ ከቋጥኝ አፈለቀ፤ ውሃን እንደ ወንዝ አወረደ።