በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።
ሆኖም ጩኸታቸውን በሰማ ጊዜ፣ ጭንቀታቸውን ተመለከተ፤
በደላቸውንም እስኪያውቁ ድረስ፣ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤ ፊቴን ይሻሉ፤ በመከራቸውም አጥብቀው ይፈልጉኛል።”
“እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ በዚህ ሰው ነፍስ ምክንያት አታጥፋን፤ የዚህ ንጹሕ ሰው ደምም በእኛ ላይ አይሁን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የወደድኸውን አድርገሃልና” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው ቀሰቀሱትና፣ “ጌታ ሆይ፤ ጠፋን፤ አድነን!” አሉት።